ራዕይ
በዞናችን የሚገኙ ሁሉም የልማት ኃይሎች የማስፈፀም፣የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅም ጎልብቶ፣ ዞናችን ኢኮኖሚው ያደገ ማኅበራዊ ችግር የሌለበት፣ የዲሞክራሲ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሆኖ ማየት፡፡
ተልዕኮ
የወጡትና የሚወጡት ፖሊሲዎች ስትራቴጅዎች ሕጎች፣ደንቦችንና መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ ሁሉም አስፈፃሚ እና ፈፃሚ አካል የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ተገቢዉን ድጋፍ በማድረግ ለተገልጋዮች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት በዞናችን ውስጥ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማጎልበት ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚደረገው ጥረት በተደራጀና ስልታዊ በሆነ መንገድ መደገፍና ለውጤት ማብቃት፡፡
እሴቶች
- የመንግስት አዋጆች፣ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎች፣መመሪያዎች፣ደንቦችና አሰራሮችን ጠንቅቆ በማዎቅ ለሁሉም አካል ግልፀኝነትና ተጠየቒነት የተሞላበት አሰራርን በመከተል ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
- በመልካም አስተዳደር እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት ተግተን እንሰራለን
- በጽ/ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በማድረግ ካላስፈላጊ ቢሮክራሲያዊ ውጣ ውረድ የፀ ዳ አሰራር መርህን እንከተላለን
- ተግልጋዩን ህብረተሰብ በቅንነት፣በታማኝነትና በትጋት እናገለግላለን
- ብቃት ያለው ዞናዊ አመራር ለመፍጠር ጠንክረን እንሰራለን
- ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በስራ እናረጋግጣለን፣
- ፍትሃዊ የሆነ ህግ እንዲወጣና ተግባራዊ እንዲሆን እንሠራለን፣
- የህግ የበላይነትን እናከብራለን፣
- የባለጉዳዮቻችንን ጥያቄ በጥሞናና በትህትና እናዳምጣለን ፣ በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፣
- በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሥርዓተ ጾታ መርህን እንከተላለን፣
- የሕብረተሰቡንና የመ/ቤቱን ሠራተኞች ዲሞክራሲያዊ ተሣትፎ ያረጋገጠ አሰራር እንከተላለን፣
- የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት ጠንክረን እንሠራለን፣
- ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰፍን እናደርጋለን።
- የግለሰብና የቡድን መብትን እናከብራለን፣
የስራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
- የሥራ መደቡ መጠሪያ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ
የሥራው ደረጃ XIV
- የስራ መደቡ ዋና አላማ፣ከስራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
- የስራ መደቡ ዋና አላማ፡-
የቡድኑን ስራወች በመምራትና በማስተባበር፣የመረጃ ስርዓት (የድረገጽ እና የሌሎች ሶፍትዌሮች/ዳታቤዞች እንዲለሙ ማድረግ፣አፈጻጸማቸውን በመከታተልና በመገምገም፣የመረጃ አውታር(ኔትወርክ) ግንባታና ማስተዳደር ስራን ውጤታማ በማድረግ የተቋሙን አሰራር ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ነው፡፡
- ከስራ መደቡ የሚጠበቁ ውጠየቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡- በዞኑና በስሩ ባሉ ወረዳወች መከናወን ያለባቸው ተግባራትን መለየትና የዘርፉን ስራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ውጤታማ ማድረግ፡፡
- የዞኑን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ በዞኑ ከሚገኙ መስሪያቤቶች ተልዕኮ ጋር የሚጣጣም የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ ና መሪ እቅድ መዘጋጀቱን ይከታተላል፡፡ በየጊዜውም እንዳስፈላጊነቱ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡
- በዞኑ ስር ያሉ ወረዳወች የጠራ ዕቅድ እንዲያቅዱ ይከታተላል፣ይደግፋል፡፡
- ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
- የዘርፉን ዝርዝር ተግባራትን ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ ይወስናል፣ አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- በስሩ የሚገኙ ባለሙያወችን ይደግፋል፣ይቆጣጠራል፣ይከታተላል፣ይገመግማል፣በየወቅቱ ይመዝናል፣በምዘናው ውጤት መሰረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
- በተቋሙ የበላይ ሀላፊወች የሚሰጠው የስልጣን ውክልና መሰረት በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ወይም የሚሰጡ ውሳኔወችን ተግባራዊነት ይከታተላል፡፡
- በመ/ቤቱ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ ማሻሻያና ማስፋፊያ የሚፈልጉ አዳዲስ ፍላጎቶች ሲኖሩ የጥናት ቡድኖች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ይከታተላል፡፡
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን አሰራር በኮምፒውተር የታገዘ ለማድረግ በተጠናና በተቀናጀ መንገድ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ ያደርጋል፣ይደግፋል፣ይከታተላል፡፡
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን ድረ-ገጽ በማደራጀትና አዳዲስ አሰራሮችን በየጊዜው በማካተት ትክክለኛና ወቅታዊ የመረጃ ፍሰት ለተጠቃሚወች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
- በመረጃ ቋቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋወችን በመለየት ለመከላከል ወቅታዊ የሆኑትን የመከላከል ሶፍትዌሮችና የሴኩሪቲ ሲስተሞችን ያደራጃል፣ተግባራዊ መሆቸውን ይከታተላል፡፡
- ተግባራዊ የሆኑ ሲስተሞች ባካፕ እንዲሁም የይለፍ ቃልና መሰል መረጃወች በ አግባቡ እንዲያዙ ያደርጋል፡፡
- የመስሪያቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት፣የመረጃወች፣የሀርድዌርና የሶፍትዌር፣የዳታ ሴንተር እና አጠቃላይ የ አይሲቲ ሃብቶች ደህንነት የሚጠበቅበትን መንገድ ፖሊሲ ይቀርጻል፣ያዘጋጃል፣ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
- የስምምነት ሰነድ እና የመረጃወችን ቅጂ በአግባቡ መያዙን ክትትል ያደርጋል፡፡
- የአይሲቲ ፕሮጀክቶችን ያቅዳል መፍትሄ አቅራቢ ድርጅቶችን ለመጋበዝና ለመምረጥ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ለማዘጋጀት በሚደረገው ሂደት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን ያስተዳድራል፡፡
- በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሰሚናሮችና በመሳሰሉት ስብሰባወች ላይ መ/ቤቱን በመወከል ይሳተፋል፡፡
- የዘርፉን ሰራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሰረት በስነምግባር ና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (coaching) ስራ ያከናውናል፣አስፈላጊ የስራ ግብአቶችን እንዲሟሉላቸው ያደርጋል፡፡
- የዘርፉን ወቅታዊ የስራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፡፡
ውጤት 2፡–የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራወችን መከታተል፡
- የዞኑን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ፍላጎት ጥናትን በበላይነት ይመራል፡፡
- በዞንና በስሩ ባሉ ወረዳወችና ቀበሌወች አገልግሎት የሚሰጡ የወረዳኔት፣ስኩልኔት፣የሁለገብ መገናኛና መረጃ ማዕከላት፣የሽቦአልባ የመገናኛ አገልግሎት፣የማህበረሰብ ሁለገብ ማዕከላትን በበላይነትይከታተላል፣ይደግፋል፣ወቅታዊ መረጃ በመያዝ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
- ከክልል በውክልና የሚሰጡ ስራወችን ያከናውናል(የሙያ ብቃት ማረጋገጫና ዕድሳት ወዘተ)፣
- አዳዲስ እና ነባር የኔትወርክ ሲስተሞች የጥራት ደረጃ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ መንገዶችን ይቀይሳል
- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሲፈቀዱ ጥራታቸውን ጠብቀው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መተግበራቸውን ክትትል ያደርጋል፡፡
- የዞኑን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮወችን በመቀመር ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
- የዞኑን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- የዞኑን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚውሉ የሶፍትዌርና ሃርድዌር መሳሪያወች ስፔስፊኬሽን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣በትክክል መስራታቸውንና አገልግሎት ላይ መዋላቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡
ውጤት 3፡– የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአሰራር ስርዐቶች በአግባቡ መዘርጋታቸውን ማረጋገጥ
- በዞኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፡፡
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማት የዲጂታል ቴክኖሎጂ (email,internet,etc) ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሰራተኞች የሚመጥን መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ስልጠና መዘጋጀቱንና ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፡፡
- በ ሶፍትዌርና መሰረተ ልማት ላይ ለዞንና ወረዳ ባለሙያወች የአቅም ግንባታ ስልጠናወችን ያመቻቻል፣ያስተባብራል፣ይከታተላል፣ይደግፋል፡፡
- የሚዘጋጁ የስልጠና ማንዋሎች ይገመግማል፣ማስተካከያ በማድረግ የመጨረሻ ቅርጻቸውን እንዲይዙ ያደርጋል፡፡
- የዞኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት አሰጣጥ በተጠቃሚወች እንዲገምገም ያደርጋል፡፡
- ከተጠቃሚወች የሚነሱ የ አሰራር ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- ኮምፒውተራይዝ ተደርገው ስራ ላይ የዋሉ ሲስተሞችን በየጊዜው አፈጻጸማቸውን በመገምገም አስፈላጊው ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ክትትል ማድረግ፡፡
- ስለተከናወኑ ተግባራት ስላጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም ስለተወሰዱ እርምጃወች ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
- የስራው ባህሪ መገለጫወች
3.1 የሥራ ውስብስብነት
- ስራው የመስሪያቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃላይ ተግባራትን ማቀድ፣ማስተባበር፣መከታተል፣ማስፋፋትና መማስተዳደር፣በየጊዜው ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ ማድረግ፣ምርጥ ተሞክሮወችን በመቀመር ተግባራዊ ማድረግ፣በከፍተኛ ደረጃ የሚያጋጥሙ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ችግሮች፣የመረጃ ቋት ደህንነት ስጋቶችን በመለየት መፍትሄ እንዲሰጥ ማድረገ እንዲሁም በ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየተከታተለ እንዲፈቱ ማድረግ፣ከቴክኖሎጂውና ከጊዜው ጋር የሚራመድ እውቀት ና ክህሎት መገንባት፣አሰራሮችንና መመሪያወችን ማሻሻል፣የ አይ.ሲ.ቲ ፖሊሲ ሃሳቦችን ማመንጨት፣ጥናቶችን እንዲጠኑ ማድረግ፣አለማቀፋዊ ተሞክሮችን በማሰባሰብ ከ መ/ቤቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ማቅረብ ይጠይቃል፡፡በተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘጋጂተው የሚቀርቡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፍላጎቶች(network expansion and upgrade,software and database need assessment) ከተቋሙ ፍላጎት ጋር አለመጣጣምና የሥምምነት ውሳኔ አለማግኘት፣በፕሮጄክት የሚሰሩ ስራወች በጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት ለፕሮጄክቱ ግብዐትየሚሆኑ ሶፍትዌሮችና ሀርድዌሮች ከገበያ ውጭ መሆን፣በፕሮጄክት የሚሰሩ ስራወች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት አለመሆን በስራ ክንውን ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆኑ እነዚህን ችግሮች ከተቋሙ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣሙ በማድረግ፣ፕሮጄክቶች በተያዘላችው የጊዜ ገደብ በወቅቱ እንዲያልቁ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ እንዲሁም ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው የሚያለቁበትን መንገድ በመቀየስ ይፈታል፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ስራው የሚከናወንበት አግባብ
- ስራው የዳይሬክቶሬቱን እቅድና የመስሪያቤቱን የ አይ.ሲ.ቲ ፖሊሲና መመሪያ፣የዘርፉን የአሰራር መርሆዎች መሰረት በማድረግ ይከናወናል፡፡
3.2.2 ስራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
- ስራው የዳይሬክቶሬቱን ስራ ውጤታማ ከማድረግና የዞኑንና በስሩ ያሉ ወረዳወችን ግብ ስኬት ለማሳካት ካደረገው አስተዋጽኦ አንጻር በአጠቃላይ ክትትልና ድጋፍ ይደረግበታል
3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለስራ ውጤት/Responsibility for impact/
- ስራው የመ/ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃላይ ተግባራትን ማቀድ፣ማስተባበር፣መከታተል፣ማስፈፋትና ማስተዳደር፣በየጊዜው ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ ማድረግ፣ምርጥ ተሞክሮወችን በመቀመር ተግባራዊ ማድረግ፣በከፍተኛ ደረጃ የሚያጋጥሙ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ችግሮች፣የመረጃ ቋት ደህንነት ስጋቶችን በመለየት መፍትሄ እንዲሰጥ ማድረግ እንዲሁም በአፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየተከታተለ እንዲፈቱ ማድረግ፣ከቴክኖሎጂውና ከጊዜው ጋር የሚራመድ እውቀት ና ክህሎት መገንባት፣አሰራሮችንና መመሪያወችን ማሻሻል፣የ አይ.ሲ.ቲ ፖሊሲ ሃሳቦችን ማመንጨት፣ጥናቶችን እንዲጠኑ ማድረግ፣አለማቀፋዊ ተሞክሮወችን በማሰባሰብ ከ መ፣/ቤቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ማቅረብ ሲሆን እነዚህ ተግባራት በአግባቡ ባይፈጸሙ የመ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአገልግሎት አሰጣጡና /በመ/ቤቱ የአሰራር ቅልጥፍናና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንዲሁም በተቋሙ ግብ ስኬት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለምስጢራዊ መረጃ፣
- የይለፍ ቃሎች/password/ ፕሮግራሞችንና ፋይሎችን፣የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ጉዳዮችን የተመለከቱ የግዢ ጨረታን በሚመራበት ጊዜ በምስጢር መያዝ የሚጠይቅ ሲሆን የምስጢሩ መባከን በመ/ቤቱ፣በስራ ክፍሎችና ከባለድርሻ አካላት(ኮንትራክተሮች፣አማካሪወችና አበዳሪ ድርጅቶች)መሃከል ከፍተኛ ቅሬታን/አለመግባባትን ሊፈጥር ይችላል፡፡እንዲሁም መ/ቤቱ ማግኘት የሚገባውን ገቢ ሊያሳጣው ይችላል፡፡
3.4 ፈጠራ
- የተሸሻሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አሰራሮችን መዘርጋትና ማልማት፣በየጊዜው ተለዋዋጭ ከሆነው ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመላመድ የአሰራር ማሻሻያወችን ማድረግ የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ አዳዲስ ችግር ፈቺ የሆኑ የአሰራር ዘዴወችን በማመንጨትና በመቀመር በስራ ላይ ማዋል ይጠይቃል፡፡
3.5 የሥራ ግንኙነት/work communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
- ስራው በመ/ቤቱ ውስጥ ከቅርብ ሃላፊው ፣በቡድኑ ስር ካሉ በተለያየ ደረጃ ከሚገኙ ባለሙያወች፣ዳይሬክተሩ ስር ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር እንዲሁም መ/ቤቱ ከሚገኙ ሌሎች ዳይሬክቶሬቶችና ቡድኖች ጋር እንዲሁም ከ መ/ቤቱ ውጭ አገልግሎት ከሚፈልጉ ተገልጋዮች፣በ አገሪቱ ካሉ ባለድርሻ አካላት/ተቋማት(ኮንሰልታንቶችና ኮንትራክተሮች)ባለሙያወች ሃላፊወች ጋር ግንኙነት ማድረግ ይጠይቃል፡፡
3.5.2የግንኙነቱ አላማ
- የ አሰራር መመሪያ ለመቀበልና ለመስጠት፣ምክክር ለማድረግ፣አገልግሎት ለመስጠት፣የተቋሙን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፍላጎት ለመለየት፣የጥናት ስራወችንና የትግበራ ሂደትን ከተለያዩ ክፍሎች ጋር ለማቀናጀት፣የበላይ አመራሩን የአዳዲስ ሲስተሞች ዲዛይኖች ጥናት ፕሮጀክቶችን ያላቸው ጠቀሜታ በማሳመን ለማጸደቅ፣አዳዲስ የሲስተም ዲዛይን ስራ ላይ ለመወያየት፣በፕሮጀክት ፕሮፖዛሉ መሰረት የተጠና መሆኑን ለመገምገም፣በስራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት መሰራታቸውን ለመከታተል ነው፡፡
3.5.3 ግንኙነቱ ድግግሞሽ
- ከስራ ሰዐቱ እስከ 50 በመቶ ይሆናል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሰው ብዛት
- በስሩ ያሉ ባለሙያወችንና በዞኑ ስር ያሉ የወረዳ አይ.ሲ.ቲ ባለሙያወችን ያስተባበራል፣ይመራል፡፡
3.6.1.2 የኃላፊነት ዓይነትና ደረጃ
- ስራው የስራ መመሪያ ለመቀበል፣ለመስጠት፣ሪፖርት ለመቀበልና ለመስጠት፣ለመወያየት፣አፈጻጸም ለመገምገም፣በጋራ ለመስራት፣የኮምፒውተር እና የመረጃ አውታር ጥገናና ክትትል ድጋፍ ለመስጠት፣ዘመናዊ አሰራር እንዲኖራቸውና የተፋጠነ አገልግሎት እንዲሰጡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች ልማትና አገልግሎት እንዲተገበር ለመረገፍና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት፣አሰራሮችን ለመፈተሸ፣ቅንጂታዊ ስራወችን ለማከናወን፣በ አቅም ግንባት ዙሪያ ድጋፍ ለማግኘት ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
- የለበትም
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
- ስራውን ለማከናወን እንደ ኮምፒውተሮች፣የኔትወርክ መሳሪያወች፣ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣Yለሙ ፕሮጀክቶችን፣የመሳሰሉትን በጠቅላላ ድምራቸው እስከ ብር 2000.00 //የሚገመቱ ንብረቶች በ አግባቡ የመያዝና የመጠቀም ኃላፊነት አለበት፡፡
3.7 ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
- ስራው የመመ/ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስራወች በማስተባበርና በመከታተል ውጤታማ ማድረግ፣የስራ ዕቅድና ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፣ምርጥ ተሞክሮወችን በመቀመር ተግባራዊ ማድረግ፣የሚያጋጥሙ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ደህንነት ስጋቶችን በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦችን ማቅረብ እንዲሁም በአፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየተከታተለ መፍታት የሚጠይቅ ሲሆን እንዲሁም ስራው የአጠቃላይ የተለያዩ ሲስተሞችን ዕቅድ፣ስፔስፊኬሽን፣ዝርዝር ፊዚቢሊቲ ጥናት፣ፕሮጀክቶችና ፕሮፖዛሎችን መገምገምና መከታተል፣የሲስተም ችግሮችን እንዲለዩ የማድረግና የመፍትሄ ሃሳብ፣ማመንጨት፣የስራ አፈጻጸም ውጤት ለመሙላት ከፍተኛ የአዕምሮ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ከስራ ጊዜው እስከ 70 በመቶ ይሆናል፡፡
3.7.2 ስነልቦናዊ ጥረት
- ስራው ቡድኖቹን አስተባብሮ ማሰራት፣ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ጥናትን በጋራ ማካሄድ፣የወቅቱን ቴክኖሎጂ ደረጃና ተለዋዋጭነት ተከትለው እንዲከናወኑ የማድረግ ሂደት የሚኖረው የስራ ጫና ተቋቁሞ፣ከተገልጋዮች ለሚቀርቡ ጥያቄወች ምላሽ መስጠት የሚጠይቅ ሲሆን ከሃሳብ ልዩነት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ግጭት ስሜትን ተቆጣጥሮ በ ትዕግስት፣በርጋታ፣ተግባብቶ በመስራት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የስነልቦና ዝግጁነትን ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
- ስራው የቡድኖቹን ስራወች ዕቅድና አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦችንና ተሞክሮወችን መጻፍ፣ከዘርፉ ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ የጥናት ጽሁፎችን ማንበብ፣ከመስሪያቤቱ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፍላጎት ጋር የተያያዙ የጥናት ጉዳዮችን ማየት የሚጠይቅ ሲሆን በጣም ከፍተኛ የእይታ ትኩረትን የሚጠይቅና በዓይን ላይ የሚያስከትለው ድካም በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ይህም ከስራ ጊዜው ከ 90 በመቶ በላይ ይሆናል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
- ስራው 75 በመቶ በመቀመጥና 25 በመቶ ለማስተባበር በመንቀሳቀሰ የሚከናወን በመሆኑ የአካል ጥረትን አይጠይቅም፡፡
3.8 የሥራ ሁኔታ
3.8.1 ስጋትና አደጋ
- ስራው የአደጋ ተጋላጭነት በሌለበት ሁኔታ የሚሰራ ነው፡፡
3.8.2 የሥራ አካባቢ ሁኔታ፣
- ስራው በሚከናወንበት ወቅት እምብዛም የጤና ጠንቅ የለበትም፡፡
የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡-የኔትወርክ አድሚኒስትሬተር IV
የሥራው ደረጃ XIII
የሥራ መደቡ አላማ ዋና ዓላማ ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ
በዞኑ ለሚገኙ ተቋማት የኔትወርክ መሰረተ ልማት በማደራጀትን በስርዓት በማስተዳደር ፈጣንና አስተማማኝ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማስቻል፡፡
ከስራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን የኔትወርክ መሰረተ ልማት ስራወችን ማስተዳደር፡፡
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን የኔትወርክ ስራ ያቀናጃል፣ያስተዳድራል፣ይከታተላል፣
- አዲስ የኔትወርክ ዝርጋታ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን የወጪ ግምት፣ጊዜና የሰው ኃይል ዕቅድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
- የሀርድዌርና የሶፍትዌር ጥገና ያከናውናል፣ጥገናው በትክክል መከናወኑን ያረጋግጣል፣ቅድመ መከላከል ስራ ያከናውናል፣
- የደንበኞች ጥያቄ ለመቀበል የፍላጎት ጥናት ያካሂዳል፣ዝርዝር ስፔስፊኬሽንና ተግባራት አጥንቶ ያወጣል፣ቴክኒካል ግምገማ ያካሂዳል፣ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት መቅረቡን ያረጋግጣል፣
- በዞኑ ስር ለሚገኙ ወረዳዎች የመስክና የመስመር ላይ/online/ ድጋፍ ይሰጣል፣
- በዞኑና በየወረዳና በቀበሌ የሚገኙ የወረዳኔት የገጠር ሁለገብ መገናኛና የመረጃ አገልግሎት፣የገጠር ሽቦ አልባ ስልክ አገልግሎት መስጠት፣
- የፍቃድ ዕድሳትና ብቃት ማረጋገጫ ይሰራል፣ይከታተላል፣ይደግፋል፣
- የኔትወርክ ሶፍትዌሮችን መጫን፣ለአገልግሎት ምቹ /ኮንፊገር / እንዲሆኑ ማድረግ፣
- በዞን ባሉ ተቋማት በኔትወርክ መሰረተልማት ላይ ለተጠቃሚዎች ድጋፍ መስጠት፣ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናች መስጠት፣
- በኔትወርክ ሲስተም ላይ ችግር ሲፈጠር ችግሮችን መፍታት፣
- በኔትወርክ መሰረተ ልማት የሚመለከቱ ሰነዶችና ሶፍትዌሮችን አደራጅቶ መያዝ፣
- በኔትወርክ አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ ባለሙያወች ስልጠና ይሰጣል፣
ውጤት 2፡- የኔትወርክ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ጥናቶችን ማካሄድ ፡፡
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን የወደፊት የሥራ ስፋት መሰረት በማድረግ የኔትወርክ ሲስተም አዲስ ለመዘርጋት፣ለማሻሻል ወይም ለማስፋፋት በጥናት ላይ የተመሰረተ ሃሳብ ማቅረብ ፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፣
- በኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ ጥናትና ምርምር ማከናወን፣ችግሮችንም በመለየት ከመፍትሄ ሃሳቦች ጋር ለውሳኔ ማቅረብ፣ሙያዊ የምክር አገልግሎት መስጠት፣
- በየደረጃው ያሉ ባለሙያወች የሚያቀርቧቸው የኔትወርክ መሰረተ ልማት የጥናት ሪፖርቶችንና የሥራ ውጤቶችን መመርመር ፣ማሻሻል፣የውሳኔ አስተያየት ማቅረብ፣
- በዞኑ የሚገኙ አዲስ የሚቋቋሙ የሥራ ክፍሎች ወይም ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ከነባር የኔትወርክ መሰረተ ልማት ጋር የሚገናኙበትን ሲስተም ማጥናት፣የኔትወርክ ዝርጋታ ተግባራትን በበላይነት ማከናወን፣
- ዘመናዊ የኔትወርክ አሰራር ለመተግበር እንዲቻል ምርጥ ተሞክሮወችን መቀመር፣ተግባራዊ እንዲሆን የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፣
ውጤት 3፡- የኔትወርክ ሲስተም ደህንነት መጠበቅና የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት፡፡
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን የኔትወርክ መሰረተ ልማት የደህንነት ፖሊሲና የአጠቃቀም ዝርዝር መመሪያወችን፣የአጠቃቀም ቴምፕሌቶችንና ማኑዋሎችን ማዘጋጀት፣
- ከኔትወርክ ሲስተም ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃወች Backup መያዝ፣
- የኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል እንዲቻል የ Disaster recovery plan ማዘጋጀት፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፣
- የኔትወርክ ሀብት ምስጢራዊነቱን እንዲጠበቅ የይለፍ ቃል/ፓስወርድ/ በሚስጥር መያዝ፣
- የኢንፎርሜሽን ደህንነት ስጋቶችን በየጊዜው ተከታትሎ ከመፍትሄ ሃሳቦች ጋር ለኃላፊው ማቅረብ፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፣
- በተቋማትና በባለድርሻ አካላት መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ልውውጥ የሚደረግበትን ሲስተም መዘርጋት፡፡
ውጤት 4. በኔትወርክ አጠቃቀም ላይ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፡፡
- በዞን በሚገኙ ተቋማት የኔትወርክ መሰረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ የሶፍትዌርና የሃርድዌር መሳሪያወች ስፔስፊኬሽን ማውጣት፣ተፈጻሚነቱን መከታተል፣
- የመስሪያቤቱ ሰራተኞችና ተጠቃሚወች የኔትወርክ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡና በብቃት መጠቀም እንዲችሉ ማንዋል ማዘጋጀትና አግባብ ካላቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፣
- የኔትወርክና የጥገና መረጃወችን ማደራጀት፣ለሚመለከተው አካል መላክ፣
ውጤት 5. ወቅታዊ ዕቅድና ሪፖርት ማዘጋጀትና መገምገም
- ለኔትወርክ አስተዳደር ስራ ዕቅድ ዝግጅት የሚያገለግሉ መረጃወችን አቀናብሮ ማቅረብ፣
- የስራ ሂደቱ ዕቅድ ዝግጅት ላይ ግብዓት መስጠት፣ማዘጋጀት፣ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ፣
- የስራ ሂደቱን ዕቅድና መርሃ ግብር መሰረት በማድረግ፣ወርሃዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፣አፈጻጸሙን መገምገም፣ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት መፍትሄዎችን ማስቀመጥ፣
- ወቅታዊ ሪፖርት ማዘጋጀት ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ፣መረጃ የመያዝና የማደራጀት ስራን መስራት፣
የሥራ ዝርዝር መግለጫ
የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡-የኔትወርክ አድሚኒስትሬተር III
የሥራው ደረጃ XIII
የሥራ መደቡ ዋና ዓ ላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
የሥራ መደቡ አላማ
የስራ መደቡ ዓላማ ፡-
የዞኑን/የወረዳዎችን የኔት ወርክ መሰረተ ልማት በማደራጀትና በስርዓት በማስተዳደር ፈጣንና አስተማማኝ የመረጃ ልውወጥ እንዲኖር ማስቻል ፡፡
ከስራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡– በዞን /በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት የኔትወርክ መሰረተልማትና ጥገና ስራዎችን ማከናዎንና ማስተዳደር
- የመስሪያ ቤቱን የኔትወርክ ስራን ማቀናጀት፣ ማስተዳር ፣ መከታተል ፣
- የኔትወርክ ሲስተሙ ከሌሎች ስራዎች ጋር ተቀናጅቶ አገልግሎት የሚሰጥበት ተግባራት ማከናወን፣
- የኔትወረወክ ሲስተሙን አጠቃቀም በግልጽ የሚማሳይ ዶክመትና ማልዋል ማዘጋጀት ፣
- በዞኑና በወረዳዎች ለሚገኙ ተቋማት ሀርድዌርና ሶፍትዌር ጥገና ማከናወን ፣ጥገናው በትክክል መከናወኑን ማረጋገጥና ፣ቅድመ መከላለል ስራ መስራት፣
- በዞኑና በወረዎች የሚገኙ ተቋማት ጥያቄ በመቀበል ፣የፍላጎት ጥናት ማካሄድ፣ዝርዝር ስፔስፊኬሽንና ተግባራት አጥንቶ ማውጣት ፣ ቴክኒካል ግምገማ ማካሄድ ፣በስፔስፌኮሽኑ መሰርት መቅረቡን ማረጋገጥ ፣
- በወረዳዎች የሚገኙ ወረዳኔቶችኖችንና ስኩልኔት፣መከታተልና መደገፍ፣
- በወረዳ ደረጃና በቀበሌ የተደራጁና የሚደራጁ የገጠር ሁለገብ መገናኛ የመረጃ አገልግሎት መከታተልና መደገፍ
- የገጠር ሽቦ አልባ ስልክ አገልግሎት መከታተልና መደገፍ፣
- በየወረዳዎች የፍቃድ ብቃትና ማረጋገጫና እድሳት ስራ እንዲሰራ መከታተልና መደገፍ፣
- በዞኑ ባሉ ተቋማት በኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ ለተጠቃሚዎች ድጋፍ መስጠት ፣የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠት፣
- የኔትወርክ ሲስተም ላይ ችግር ሲፈጠር ችግሮቹን ለይቶ በማወቅ የመፍትኔ ሃሳብ ማቅረብ ፣
- ኔትወርክ መሰረተ ልማት የሚመለከቱ ሰነዶችና ሶፍት ዌሮችን አደራጅቶ መያዝ ፣
- የመስክና የመስመር ላይ/online/ ድጋፍ መስጠት፣
ውጤት 2. የኔትወርክ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ጥናቶችን ማድረግ ፡፡
- ኔትወርክ ዘርፍ በየጊዜው የሚወጡ አዳዲስ ግኝቶችንና የምርምር ውጤቶችን ከተለያዩ ምንጮች ማሰባሰብ ፣ የተሰበሰበው መረዳ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣
- የኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ ጥናት ያካሂዳል፣ሙያዊ የምክር አገልግሎት መስጠት
- የኔትወርክ ሲስተም የደህንነት ፖሊሲና የአጠቃቀም ዝርዝር መመሪያዎች ረቂቅ ማዘጋጀት ፣
- በዞኑ የሚገኙ መስሪያ ቤቶችን የወደፊት የስራ ስፋት መሰረት በማድረግ የኔትወርክ ሲስተም አዲስ ለመዘርጋት፣ ለማሻሻልና ለማስፋፋት በጥናት ላይ የተመሰረተ ሃሳብ ማቅረብ ፣
ውጤት 3. በዞን/በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት የኔትወርክ ደህንነት መጠበቅና የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት ፡፡
- በዞን/በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት ኮምፕውተር ኔትወርክ ሶፍትዌሮችን ይጭናል ፣ለአገልግሎት ምቹ /ኮንፈርት / እንዲሆን ማድረግ ፣
- የኔትወርክ ሃብት ሚስጥራዊነቱን እንዲጠበቅ የይለፍ ቃል /ፓስ ወርድ /ማድረግና በሚስጢር መያዝ፣
- ከኔትወርክ ሲስተም ጋር ተያያዝነት ያላቸውን መረጃወች መያዝ ፣
- የኔተውርክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ጎዳት ለመከላለል እዲቻል የDisaster recovery plan ማዘጋጀት፣
- በኔትወርክ ግንኙነት ምክንያት በሲስተም ላይ የሚደርሱትን ችግሮች እየተከታተለ መመዝገብ፣ችግሩን ማስተካከል፣እንደ አስፈላጊነቱ ለሃላፊው በማቅረብ መፍትሄ እዲሰጥ ማድረግ ፡፡
ውጤት 4. በዞንና /በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት በኔትወርክ አጠቃቀም ላይ ሙያዊ ድጋፍ መስጠትና መከታተል ፡፡
- የተዘረጋ ኔትወርክን እርስ በርስ የሚያገናኝ ሶፍትዌር -ኔትወርክ ፐሮቶኮል፣ መረጣ ላይ እገዛ ማድረግ ፣
- ልዪ ልዩ የዳታ ኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን መለየት፣መምረጥ በኔትወርክ መሰረተ ልማት ያሉትን ለውጦች በመከታተል በተግባር ሊውሉ የሚችሉበትን ሃሳብ ማቅረብ፣
- በዞን/በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት የኔትወርክ መሰረተ ልማት በሙሉ አቅሙ አገልግሎች መስጠቱን መከታተል ፤የቅድመ ጥንቃቄ ዝግጅት ማድረግ፣አስፈላጊ ሲሆን የእርምት እርምጃ መውሰድ ፡፡
- ተጠቃሚዎች የኔትወርክ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡና በብቃት መጠቀም እንዲችሉ በማንዋል ዝግጂት ላይ ያሳትፋል ፣የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፣
ውጤት 5. ወቅታዊ እቅድና ሪፖርት ማዘጋጀትና መገምገም ፡፡
- የኔትወርክ አስተዳደርና ስራ እቅድ ዝግጂት የሚያገለግሉ መረጃዊችን አጠናክሮ ማቅረብ ፣
- የስራ ሂደቱ እቅድ ዝግጂት ላይ ግብዓት ይሰጣል ፣ያዘጋጃል ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ ፣
- የስራ ሂደቱን ዕቅድና መርሃ ግብር መሰረት በማድረግ ፣ወርሃዊ ዕቅድ ያዘጋጃል ፣አፈፃፀሙን ገምግሞ ፣ጠንካራና ደካማ ጎኖቹን በመለየት መፍትሄዎችን ማስቀመጥ ፣
- ወቅታዊ ሪፖርት ያዘጋጃል ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ ፣
- መረጃ የመያዝና የማደራጀት ስራን ይሠራል፣
የሥራ ዝርዝር መግለጫ
የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡- የሶፍትዌር ሲስተም አድሚኒስትሬተር III
የሥራው ደረጃ XII
የሥራ መደቡ ዋና ዓ ላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
የሥራ መደቡ አላማ:-
በሲስተም ልማት ላይ ዝርዝር የሲስተም ጥናት በማከናወን የዞኑን የመረጃ ስርዓት ማጎልበትና ቀልጣፋ ማድረግ ፡፡
- የስራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1. በአዳዲስ የመረጃ ሲስተሞች ላይ ጥናት ማካሄድና የመረጃ ፍሰት ስርዓትን ማሻሻል፣
- በመረጃ አሰባሰብ ፣አያያዝ ፣አደረጃጀት ፣ጠቃቀም ክምችትና ስርጭት ላይ የፊዚቢሊቲ ጥናት ማካሄድ፣
- የሚሰበሰቡ መረጃዎች በሥርዓት የሚቀረፁበትን ፣የሚከማቹበትንና የሚሰራጩበትን ስልት መቀየስ፣
- ነባርና አዳዲስ የመረጃ ማሰባሰቢያ ቅፆችን ያዘጋጃል፣ማሻሻል፣አዳዲስ የመረጃ ሪፖርት ማድረጊያ ዘዴዎችን መቀየስ ፣ተግባራዊ ማድረግ፣
- ነባር የመረጃ አሰራር ዘዴዎችን ለማሻሻልና አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችን ለማስተዋወቅ የሲስተም አናሊስት ዲዛይን ስራ እንዲከናወን ሃሳብ ያመነነጫል ፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፣
- የመረጃ ልውውጥ ኡደት ከመነሻ እስከ መድረሻ ድረስ የዳታ ፕሮሰሲንግ ደንብን ተከትሎ እንዲከናወን የሲስተም ዲዛይን ማዘጋጀት፣
ውጤት 2. የሲስተም ዝግጅት ጥናት በማካኔድ የማሻሻያ ሃሳብ በማቅረብ እገዛ ማድረግ
- የሲስተም ጥናት ያካሂዳል የማሻሻያ ሃሣቦችን ማቅረብ ፣
- ከኢንፎርሜሽን ሲስተም ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ መመሪያዎች ዝግጂት ላይ መሳተፍ፣
- የሲስተም ዝግጂት ዝርዝር /specification/ መግለጫ ዶክመት ዝግጂት ላይ መሳተፍ፣
- ስለተከነወኑ ተግባራትስለአጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም ስለተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ሪፖርት ማቅረብ፣
ውጤት 3. የሲስተም ልማት ስራ ማከናወንና ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ
- ከፊደራልና ከክልል የወረዱና በተለያዩ በዞኑ በሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ የሆኑና በሂደት ላይ ያሉ ሲስተሞችን መከታተልና መደገፍ፣
- በዞኑ የሚገኙ ተቋማትን የሶፍትዌር ፣ዳታቤዝና ድረ-ገጽ ፍላጎት መለየት ፣ ዲዛይን ማዘጋጀት፣በተጠቃሚዎችና በባለሙያዎች ማስገምገም፣ማስተካከል ለተጠቃሚዎች ስልጠና በመስጠት ሶፍትዌሩን ስራ ማስጀምር፣ማስተዳደር
- በየቀኑ የዳታቤዝ ባካፕ መውሰድ ፣በዳታቤዝ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ማስተካከል፣ከአቅም በላይ ከሆነ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ ፣
- ለወረዳ ባለሙያዎች የመስክና የመስመር ላይ ድጋፍ ማድረግ ፣መከታተል፣
- በዞኑ ለሚገኙ ተቋማት የሲስተም ልማት ላይ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ ፣
- በዞኑ ለሚገኙ ተቋማት በሲስተም ልማት ዘርፍ ለሚቀጠሩ ባለሙያዎች ፈተና መፈተን ፣
ውጤት 4. ወቅታዊ እቅድና ሪፖርት ሪፖርት ማዘጋጀትና መገምገም ፡፡
- የስራ ሂደቱ እቅድ ዝግጂት ላይ ግብዓት መስጠት ፣ የራሱን ዕቅድ አዘጋጂቶ ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ ፣
- የስራ ሂደቱን እቅድና መርሃ ግብር መሰረት በማድረግ ወርሃዊ እቅድ ማዘጋጀት፣አፈጻጸሙን መገምገም ፣
- የተሰጠው የስራ ድርሻ አፈጻጻምን በየወቅቱ መገምገም፣ጠንካራና ደጋማ ጎኖችን በመለየት መፍትሄዎችን ማስቀመጥ፣
- መረጃ በመያዝና በማደራጀት ስራን መስራት
- ወቅታዊ ሪፖርት ያዘጋጃል ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ፣
የሥራ ዝርዝር መግለጫ
የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡- የኢኮቴ የመገናኛና አቅም ግንባታ ባለሙያ III
የሥራው ደረጃ XII
የሥራ መደቡ ዋና ዓ ላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
የሥራ መደቡ አላማ:-
በዞኑ ለሚገኙ ተቋማት ለበርካታ የስራ ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ ሙያዊ ቴክኒካል ስራዎች በመስራት አገልግሎቱን ፈጣን እና ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ፣
ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1. በዞን ለሚገኙ ተቋማት ለበርካታ የስራ ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ ሙያዊ ቴክኒካል ስራዎች መስራት
- በዞኑ ለሚገኙ ተቋማት ለበርካታ የስራ ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ ሙያዊ ቴክኒካል ስራዎች መስራት፣ቴልኒካል ዶክመንቶች ማዘጋጀት የመፍትሄ ሃሳብ ማመንጨት፣
- የአጠቃቀም ፖሊሲ ፣የአሰራር መመሪያ /Guideline/፣ማንዋል /user manuals/ እና ተዛማጂ ሰነዶች መሰረት አገልግሎች መስጠት፣ተግባሪዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
- የምርምር ስራዎች ሂደት በትክክልና በሚፈለገው ጥራት እየሰሩ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚደረገው ክትትል ላይ ግብዓት መስጠትና መደገፍ፣
ውጤት 2. በዞን በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት ለበርካታ የስራ ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ የማስፋፋት ስራ ይከናወናል ፡፡
- የተቀናጀ(intergrated)አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የማስፋፊያ መሪ ጥናት መስራት፣
- ከደንበኞች የሚነሱ የተለያዩ የድጋፍ ጥያቄዎች ላይ ጊዜያዊ እና ዘላቂ ቴክኒካል የመፍትሄ ሃሳብና ማብራሪያ መስጠት፣
- የቴክኖሎጂ የውይይት መድረክ ወይም ወርክ ሾፕ ማዘጋጀት፣ሙያዊ አስተያየት መስጠት/ማቅረብ፣
ውጤት 3. በዞን በወረዳ ለሚገኙ ተቋማት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ያሳድጋል፣
- በelearning መሰረተ ልማት መሰጠት የሚችሉ ስልጠናዎች ካሉ መለየት፣ መሰረተ ልማቱ እንዲዘረጋና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- የስልጠና ማዕከላትን የማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላትንና ሬዲዮ ማዕከላትን መደገፍና መከታተል፣
- የወረዳ አይሲቲ ባለሙያዎች የመስክና የመስመር ላይ (ኦንላይን )ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣መከታል፣መደገፍ፣
- የቴክኖሎጂ ስርዓትና አጠቃቀም ፣ግንዛቤ ማስጨበጫና ቅድመ ስራ ላይ ስልጠና መስጠት፣
- የስልጠና ፍላጎት መጠይቆች አሰራጭቶ በመሰብሰብ ተፈላጊው የስልጠና ዓይነቶችና ሰልጣኞችን መምረጥ፣ማሰልጠን ፣ክትትል በማድረግ ጉድለቶችን ማሟላት፣የስልጠናውን ውጤት መገምገም ፣
- በየደረጃው የኢኮቴ ሥልጠና ያስገኘውን ፋይዳ ጥናት ማጥናት፣የሰልጣኞችን መረጃ መያዝ፣
- የሰው ሃይል ልማት በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራትን መከታተል፣መደገፍ፣መገምገም፣
- በዞን ለሚገኙ ተቋማት ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በሚቀርብ ጥያቄ መመሰረት በጀማሪና መካከለኛ ደረጃ ለሚገኙ የኢኮቴ ባለሙያዎች የቅጥር ቴክኒካል ምዘና (ፈተና ) በማዘጋጀት መፈተን፣
ውጤት 4. በዞን ለሚገኙ ተቋማት ለበርካታ የስራ ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት
- ለበርካታ የስራ ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጥ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ የአሰራር ስርዓት መመሪያ ፣ማንዋል ፣ወዘተ ማዘጋጀት ፣
- የቴክኖሎጂ ስርዓትና አጠቃቀም ግንዛቤ የማስጨበጥ ስልጠና መስጠት ፣
- ተለይተው ለወጡ የስልጠና አይነቶች አጠቃላይ ይዘት ፣ተገቢውን የስልጠና አሰጣጥ ይዘት መለየት ፣ተገቢውን የስልጠና አሰጣጥ ዘዴ መምረጥ፣የሚወስዱትን ጊዜና ወጭ መገመት፣እንዲሁም የእያንዳንዱ ስልጠና አስፈላጊነት ቅድመ ተከተል መያዝ ፣
- የኢኮቴ ምርምር ውጤቶች የሚቀርቡበት አውደጥናት ማዘጋጀት፣
ውጤት 5. ወቅታዊ እቅድና ሪፖርት ማዘጋጀትና መገምገም
- ወቅታዊ እቅድ ማዘጋጀት፣የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በማጠናቀር ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ ፣
- በስራ ሂደቱ ዕቅድና መርሃ ግብር መሰረት በምድረግ ፣ሳምንታዊ እቅድ ማዘጋጀት ፣አፈጻጸሙን መገምገም ፣ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት መፍትሄዎችን ማስቀመጥ፣
- የዘርፍ እቅድ ዝግጅት ላይ ግብዓት መስጠት ፣ማዘጋጀት ፣ለኃላፊውና ለሚመለከተው አካል መላክ፣
- መረጃ የመያዝና የማደራጀት ስራ መስራት ፣