About Us

የማዕካዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ራዕይ ተልዕኮና እሴት

ራዕይ

በዞናችን የሚገኙ ሁሉም የልማት ኃይሎች የማስፈፀም፣የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅም ጎልብቶ፣ ዞናችን ኢኮኖሚው ያደገ ማኅበራዊ ችግር የሌለበት፣ የዲሞክራሲ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሆኖ ማየት፡፡

ተልዕኮ

የወጡትና የሚወጡት ፖሊሲዎች ስትራቴጅዎች ሕጎች፣ደንቦችንና መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ ሁሉም አስፈፃሚ እና ፈፃሚ አካል የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ተገቢዉን ድጋፍ በማድረግ ለተገልጋዮች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት በዞናችን ውስጥ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማጎልበት ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚደረገው ጥረት በተደራጀና ስልታዊ በሆነ መንገድ መደገፍና ለውጤት ማብቃት፡፡

እሴቶች

  • የመንግስት አዋጆች፣ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎች፣መመሪያዎች፣ደንቦችና አሰራሮችን ጠንቅቆ በማዎቅ ለሁሉም አካል ግልፀኝነትና ተጠየቒነት የተሞላበት አሰራርን በመከተል ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
  • በመልካም አስተዳደር እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት ተግተን እንሰራለን
  • በጽ/ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በማድረግ ካላስፈላጊ ቢሮክራሲያዊ ውጣ ውረድ የፀ ዳ አሰራር መርህን እንከተላለን
  • ተግልጋዩን ህብረተሰብ በቅንነት፣በታማኝነትና በትጋት እናገለግላለን
  • ብቃት ያለው ዞናዊ አመራር ለመፍጠር ጠንክረን እንሰራለን
  • ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በስራ እናረጋግጣለን፣
  • ፍትሃዊ የሆነ ህግ እንዲወጣና ተግባራዊ እንዲሆን እንሠራለን፣
  • የህግ የበላይነትን እናከብራለን፣
  • የባለጉዳዮቻችንን ጥያቄ በጥሞናና በትህትና እናዳምጣለን ፣  በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፣
  • በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሥርዓተ ጾታ መርህን እንከተላለን፣
  • የሕብረተሰቡንና የመ/ቤቱን ሠራተኞች ዲሞክራሲያዊ ተሣትፎ ያረጋገጠ አሰራር እንከተላለን፣
  • የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት ጠንክረን እንሠራለን፣
  • ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰፍን እናደርጋለን።
  • የግለሰብና የቡድን መብትን እናከብራለን፣

ዞኑን ማዕከላዊ ጎንደር መስተዳድር ዞን

የማዕከላዊ ጎንደር መስተዳደር ዞን በኢትዮጵያ የአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ጊዜ  በነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ከአሁኑ ደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን ጋር በአንድነት ተጠቃሎ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት በመባል ይጠራ በነበረው  የተጠቃለለ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ንጉሳዊው የመንግስት መዋቅር በየካቲት ወር 1966 ዓ.ም ጀምሮ በአብዮታዊ መንግስት ከተቀየረ በኋላ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት የሚለው መጠሪያ  የጎንደር ክፍለ ሃገር ተብሎ  ሲጠራ ከቆየ በኋላ በኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ ተብሎ ሲጠራ ቆይቷል ፡፡ ከዚያም የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አካባቢ እየተባለ መጠራቱ እስከ ከደርግ መውደቅ ቀጥሎ ከግንቦት 1983 ዓ.ም  በኋላ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት በክልል ሶስት መስተዳድር የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን በሚል መጠሪያ ከቆየ በኋላ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ተብሎ እንደነበር በዞኑ አስተዳደር ካለው ነባር መዝገብ ቤት ካሉ ገዥዎች አስተዳዳሪዎች ይጻጻፉባቸው የነበሩ ደብዳቤዎችና ሌሎች መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ዋና ከተማን በተመለከተ በእንደራሴዎችናገዢዎች በአስተዳዳሪዎች ጊዜ አንስቶ የመሪዎች መቀመጫ  ጎንደር ከተማ ናት፡፡በጌምደርና ስሜን ጠቅላይ ግዛትና ጎንደር ክፍለ ሀገር በሚባል መጠሪያ ጊዜ የነበረው የአስተዳደር እርከን

1. ስሜን  አውራጃ

2. ወገራ አውራጃ

3. ጎንደር ዙሪያ አውራጃ

4. ጭልጋ አውራጃ

5. ሊቦ አውራጃ

6. ደብረታቦር አውራጃ

7. ጋይንት አውራጃ ነበሩ፡፡

ማዕከላዊ ጎንደር መስተዳድር ዞን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ 14 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ አንዱና ከክልሉ በቆዳ ስፋትም ሆነ በህዝብ ብዛት ተወዳዳሪ ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ የሆነችው ታሪካዊቷ ጎንደር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ ከሆነችው ባህርዳር በሰሜን አቅጣጫ 175 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

የዞኑ አወቃቀር በ15 የገጠር ወረዳዎችና በ4 የከተማ አስተዳደሮች በ1 ሜትሮፐሊታንት ከተማ/ጎንደር ከተማ/ በ384 የገጠርና 40 የከተማ  ቀበሌዎችን  በአጠቃላይ 424 ቀበሌዎችን የያዘ ነው፡፡ ምንጭ የዞኑ ማዕ/ጎ/ዞን/አስ/ፕላንና ልማት ቡድን 2016 እትም መጽሄት

የዞኑ አዋሳኞች በሰሜን ሰሜን ጎንደርና ወልቃይት ሰቲት ሁመራ፣ በደቡብ ከደቡብ ጎንደርና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ በምዕራብ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልና ምዕራብ ጎንደር ፣ በስተምስራቅ ከደቡብ ጎንደርና ከዋግ ህምራ ዞኖች  ጋር ይዋሰናል፡፡

የዞኑ አጠቃላይ ገጽታ በአጭሩ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ13° 48’ እስከ 11° 30’ ሰሜን የኬክሮስና በ35° 13’ እስከ 38° 49’ ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የቆዳ ስፋቱ 104,329.5 ካሬ ኪ.ሜ. ይሆናል፡፡ የሚያዋስኑትም በምስራቅ- ዋግ ህምራ ዞን ፣ በምዕራብ-ምዕራብ ጎንደር፣ በደቡብ ምዕራብ–ሰሜን ጎጃም፣በሰሜን-ሰሜን ጎንደር በሰሜን ምዕራብ–ሰቲት ሁመራ ዞን እንደዚሁም በደቡብ- ደቡብ ጎንደርና ጣና ሐይቅ  ናቸው፡፡

በዞኑ በ15 የገጠር ወረዳዎችና አራት ከተማ አስተዳደሮች በስራቸውም 423 የቀበሌ አስተዳደር መዋቅሮች ይገኙበታል፡፡

በመኸር በመልማት ላይ የሚገኝ 529,571 ሄ/ር መሬት ያለ ሲሆን የምግብ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችን የማምረት አቅም አለው፡፡ የዞኑ የመሬት አቀማመጥ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ማለትም በከፍተኛና በዝቅተኛ ቦታዎች የሚመደብ ሲሆን የከፍተኛ ቦታዎች ምድብ የሚይዘው ከባህር ወለል በላይ ከ1,500 ሜትር በላይ የሆኑትን ቦታዎች ማለትም አብዛኛው የዞኑ ሰሜናዊ፣ሰሜናዊ ምሥራቅና  ምዕራብ  ክፍሎች በዚሁ ምድብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ አብዛኛው የዚህ አካባቢ ቦታዎች ሰንሰለታማና አምባ ምድሮች፣ እንደ ባንብሎ /2,750 ሜትር ከፍታ/፣ ቆልማሜ /2,496 ሜትር ከፍታ/ የመሳሰሉ ትልልቅ ተራራዎችን የሚያቅፍ ነው፡፡ የዝቅተኛ ቦታዎች ምድብ ደግሞ የዞኑን በከፊል ምስራቃዊ፣ምዕራባዊና ደቡባዊ ቦታዎች የሚያቅፍ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ያላቸው ከፍታ ከ500-1500 ሜትር ነው ፡፡ ይህ ምድብ የትልልቅ ወንዞችን፣ ተፋሰሶች የሚሸፍንና ሜዳማ የሆነ የመሬት አቀማመጥ ያለው በመሆኑ ሰፋፊ እርሻዎችን ለማካሄድ አመቺነት ያለው አካባቢ ነው፡፡

ዞኑ በሶስት ዋና ዋና የአየር ንብረት የተከፋፈለ ሲሆን 37% ያህሉ ቆላማ ፣45.2% ያህሉ ወይናደጋ እና 17.8% ደጋ የአየር ንብረት አለው ፡፡ የዞኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ42 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሲሆን ዝቅተኛው ከ10 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች ይወርዳል፡፡ የዞኑ ዓመታዊ የዝናብ መጠንም ዝቅተኛው 1,172 ሚ/ሜትር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 1,700 ሚ/ሜትር በላይ ነው፡፡ ዞኑ አንድ የዝናብ ወቅት/ የመኽር/ ተጠቃሚ ነው፡፡

ዞኑ ከ8 በላይ ቋሚ ወንዞችና የጣና ሀይቅ ባለቤትም ሲሆን በአጠቃላይ በሶስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ስር ይወድቃል፡፡ ከእነዚህ  ወንዞች ውስጥ ጣና፤ አንገረብና ጓንግ የተከዜ ገባር በመሆን ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ናቸው፡፡  ዞኑም ከነዚህ የውሃ ሃብት በተጨማሪ ከፍተኛ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችት እንዳለው ይገመታል፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚገኙና የከርሰ ምድርና የገፀ-ምድር ውሃን ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ መሬት በመስኖ መልማት የሚችል አቅም ያለው ዞን ቢሆንም እስካሁን የለማው ዝቅተኛ ነው ፡፡

በዞኑ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞች መጋቢ ወንዞችና ጣና ሀይቅ ለመስኖ ልማት ፣ የዓሣ ሀብት ልማት ለማስፋፋት እና የትራንስፖርት አግልግሎት ለማካሄድ የሚያስችል የማይናቅ የውሀ ሀብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ይሁን እንጅ እስከ አሁን በጥቅም ላይ የዋለው የውሃ ሃብት በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ለአብነት በእንስሳት ዓሳ ሃብት ልማት ከክልሉ 18.2% ድርሻ ያለው ዞን ነው ፡፡

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲን ቆጠራ መሰረት በማድረግ የዞኑ ፕላንና ልማት ስነህዝብ ቡድን (የ2018 ዓ/ም) ፕሮጀክሽን እንደሚያሳየው የዞኑ ህዝብ ብዛት 2,419,558 ወንድ 1,215,317 (50.24 በመቶ) ሴት 1,204,242 (49.75 በመቶ) እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ከዚህ ውስጥ በከተማ 415,708 (ወንድ 196,235 ፣ሴት  219,473) በገጠር 2,003,851 (ወንድ 1,019,082፣ ሴት  984,769)   የሚኖር ነው ::  ከዞኑ ህዝብ 1,302,438 ወይም 53.8 በመቶ የሚሆነው  ህዝብ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ ከ64 ዓመት  የሆኑት ምርታማ የሆነው የሰው ኃይል ሲሆን ይህ ብዛት ያለው በሥራ ሊሰማራ የሚችል የሰው ኃይል በአንድ በኩል በአጭር ጊዜ የሥራ እድል መፍጠርን የሚጠይቅ ሲሆን በሌላ በኩል ይህ ብዛት ያለው አምራች የሰው ሃይል ለአገር  ኢኮኖሚ እድገት ጥሩ የስነ ህዝብ መልካም አጋጣሚ ነው፡፡

በአጠቃላይ ዞኑ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር ፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሀ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው፡፡ በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በዞኑ ለገበያ የሚውሉ የተለያዩ የምግብ፤ የኢንዱሰትርና ኤክስፖርት (የብዕር፣የአገዳ፣ የጥራጥሬና የቅባት) እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል ፡፡ የእንስሳት ሃብታችን ስንመለከት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአጠቃላዩ የእንስሳት ሃብት 17.4 በመቶ የሚሸፍን ዞን ነው፡፡

በዞናችን ሰሊጥ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሚባሉ የኤክስፖርት ምርቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ለአገራዊ ምርት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው። ከፍተኛ ፍላጎት ያለው እና ጠንካራ የገቢ ማስገኛ አቅም ያለው በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ የኤክስፖርት ምርት ነው።

በዞናችን ምቹ የቱሪዝም ቦታዎች መካከል ጎርጎራ በሚያስደንቅ ሁኔታ የተፈጥሮ ውበት ያሉበት ተስማሚ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻ ነው። ከውበቱ በተጨማሪ በቅርቡ ይፋ የሆነው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ዘመናዊ ድንቅ ስራ የያዘ በመሆኑ ከተፈጥሮ ጋር ያዋህዳል። ይህ ዘመናዊ ሪዞርት እንደ የመዋኛ ገንዳዎች፣ ጥሩ የመመገቢያ ምግብ ቤቶች፣ የሐይቅ ዳር አምፊቲያትር እና ወደ ጣና ሀይቅ የሚዘልቅ ድንቅ የመርከብ ጣቢያ ያሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ለጎብኚዎች ልዩ የሆነ አገልግሎት እና በአስደናቂ አከባቢዎች መካከል የማይረሳ ቆይታ የሚፈጥር ልዩ የቱሪስት መነሀሪያ ነዉ፡፡

በጠቅላይ ግዛትና በዞን ደረጃ ዋና አስተዳዳሪዎች የነበሩና እስከአሁን ያሉ

ይህ መረጃ ከተጠናቀረው ቀደም ብለው ጠቅላይ ግዛቱንና በኋላም ክፍለሃገሩን ያስተዳድሩ የነበሩ መሪዎች ከተጻጻፉት ከዞኑ አስተዳደር መዝገበብ ቤት የተገኘና  አሁን በማስተዳደር ላይ ያሉት ደግሞ በቀጥታ የተገኘ መረጃ ነው፡፡ በተሟላ ሁኔታ መረጃ ያልተገኘባቸው  ክፍት ሆነዋል፡

ተ.ቁአስተዳዳሪ ስም  ማዕረግ  የአስተዳደሩ መጠሪያ  የቆይታ ጊዜ  
 1አስራተ ካሳ  ደጃዝማች  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት  1935  
2  አንዳርጋቸው መሳይ  ቢትወደድ  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ገዢ  1941 -1944  
3  አስራተ ካሳ  ደጃዝማች  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ገዢ  1945-1948  
4  ክፍሌ ዳዲ  ደጃዝማች  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ  1950  
5  አምሃ አበራ  ደጃዝማች  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ገዢ  1953-1954  
6  ክቡር  ነጋ ሃይለ ስላሴ  ደጃዝማች  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ገዢ  1955-1957  
7  ክቡር ታምራት ይገዙ  ሌ/ኮል  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ገዢ  1958-1964  
8  ነጋ ተገኝ  ሌተ/ጀነራል  በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ገዢ  1967  
9  ዳኘው ወልደ ስላሴ  አቶ  ጎንደር ክፍለሃገር አስተዳደሪ  1968  
10  እምሩ ወንዴ  ኮሎ/ል  ጎንደር ክፍለሃገር አስተዳደሪ  1969  
11  መላኩ ተፈራ  ሻለቃ  ጎንደር ክፍለሃገር አስተዳደሪ  `1970-1975  
12  ወጋየሑ ሳህሉ  አቶ  ጎንደር ክፍለሃገር  አስተዳደሪ  1978  
13  ሞላልኝ በላይ ረታ  አቶ የሰሜንጎንደር አስተዳደር አካባቢ አስተዳደሪ  1981-1982  
14  ሽፈራው እንቁ ባህር  አቶ  የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ አስተዳደሪ  1982-1984  
15  አስማማው የሱፍ  አቶ  የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ አስተዳደሪ  1984 -1985  
16  አድጎአይቸው ፀጋ  አቶ  የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ አስተዳደሪ  1985-1987  
17  አቡኔ መንገሻ  አቶ  የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ አስተዳደሪ  1987  
18  ተሰማ ገብረህይወት  አቶ  የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አካባቢ አስተዳደሪ  1988-1993  
19  ሙሌ ታረቀኝ  አቶ  የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳደሪ  1994-1998  
20  ጌታቸው ጀምበር  አቶ  የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና   አስተዳደሪ  1998-2000  
21  አገኘሁ ተሻገር  አቶ  የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና   አስተዳደሪ  2000-2003  
22  ግዛት አብዩ  አቶ  የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳደሪ  2003- 2008 ጥር  
23  ሙሉጌታ ወርቁ  ኮሚሽነር  የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳደሪ  2008 ጥር ወር ጀምሮ  
24አየልኝ ሙሉዓለምአቶየሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳደሪ   
25ብርሃኑ ጣምአለውአቶየማዕከላዊ ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳደሪ 
26ወርቁ ኃይለማርያምአቶየማዕከላዊ ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳደሪ 
27አወቀ አስፈሬአቶየማዕከላዊ ጎንደር መስተዳድር ዞን ዋና አስተደሰደሪ2016 ጀምሮ

 የዋና አስተዳዳሪው መልዕክት

ኢንፎርሜሽን ኮሚውኒኬሽን ቴክኖሎጂ በሀገራችን እድግት መሳካት ያለው ሚና ከፈተኛ መሆኑ የሚታወቅ ግልፅ እውነታ ነው፡፡በመሆኑም ይሀንን ወሳኝ የእድገትአሳላጭ መሳሪያ ለማጎልበት እና ሌሎችም እነዲጠቀሙት የማድረግ ተግባር ይጠበቃል፡፡ በዚህ ረገድ የማዕከላዊ ጎንደር አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቡድን ይህንን ድረ ገጽ በማጎልበት የመረጃ ልውውጥን ለማፋጠን እና ለዞናችን ብሎም ለሀገራችን ዕድገት መሳካት ያበረከተው አስተዋጽኦ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡በቀጣይም ይህንን ተግባር በመቀጠል ከዚህ በተሻለ መልኩ ተግባሩን ለማከናወን የበለጠ ትጋት ያስገፈልጋል፡፡በተጨማሪም በዞናችን የሚገኙ ወረዳዎች ይህንኑ ተመሳሳይ ተግባር በተጠናከረ መልኩ በማከናወን የዞናችንን የመረጃ ልውውጥ እና የቴክኖሎጂ ልውውጥ የሚፋጥaን ተግባር ለማከናወን የየራሳቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስባለሁ፡፡

በጠቅላይ ግዛትና በዞን ደረጃ ዋና አስተዳዳሪዎች የነበሩና እስከአሁን ያሉ

ይህ መረጃ ከተጠናቀረው ቀደም ብለው ጠቅላይ ግዛቱንና በኋላም ክፍለሃገሩን ያስተዳድሩ የነበሩ መሪዎች ከተጻጻፉት ከዞኑ አስተዳደር መዝገበብ ቤት የተገኘና  አሁን በማስተዳደር ላይ ያሉት ደግሞ በቀጥታ የተገኘ መረጃ ነው፡፡ በተሟላ ሁኔታ መረጃ ያልተገኘባቸው  ክፍት ሆነዋል፡፡

Scroll to Top