Public Compliant Hearing

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ተልእኮ ፤ራዕይና እሴቶች፤

 ተልዕኮ ፡-

በተገልጋዩች የሚቀርቡ ቅሬታዎችና የአስተዳደር በደሎችን በመቀበል መመርመር ውጤታማ የሆነ አስተዳደራዊ ፍትህ መስጠት ፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት መደገፈና የመረጃ ምንጭ በመሆን ማገልገል ፡፡

       ራዕይ

ግልፅነትና ተጠያቂነት የተረጋገጠበት የህግ የበላይነት የተከበረበት ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር በደለን የሚከላከል የቅሬታ ርዓት ተፈጥሮ ማየት ፣       

       እሴቶች

  • ለደንበቻችን አክብሮት አእንሰጣለን ፡፡ ቅልጥፋናንና ውጤታማ አገልግሎት እናሰፋናለን ፡፡
  • የቅሬታ አቀራረቡ ግልፅ ቀላልና ለደንበኞች የተመቸ እንዲሆን እንሰራለን ፡፡
  • የጊዜን አስፈላጊነትና ዋጋ በመረዳት አገልግሎት እንሰጣለን ቀጠሮ እናከብራለን
  • ውሳኔአችን በህግ መሰረት እንዲሆን ትኩረት እንሰጣለን የህግ የበላይነትን እናከብራለን ፡፡
  • የግልፀኝነትና የተጠያቂነት መርሆዎችን የስራችን መመሪያ ይሆናሉ ፡፡
  • የፆታ እኩልነት ለማክበርና ለማስከበር በሙሉ አቅምና ፍላጐት እንሰራለን
  • መማማርንና የቡድን ሥራ እናጠናክራለን ፡፡ እናከብራለን ፡፡
  • በትእግስት ፣ በሀቀኝነት ገለልተኛና ሚዛናዊ ሁነን ደንበኞችን እናከብራለን ፡፡

የማዕከላዊ  ጎንደር የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ደንበኞች/ተገልጋዩች

  • አስተዳደራዊ በደል የደረሰባቸው ቅሬታ /አቤቱታ አቅራቢዎች
    • በተዋረድ የሚገኙ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ አካላት
    • አገልግሎት ሰጪ የመንግስት መስሪያ ቤቶች

 የህዝብ ቅሬታ ሰሚ  የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

  • ባለጉዳዩችን በትህትና ተቀብሎ ከአድሎ በነፃ መንገድ በህጋዊ አግባብ ማስተናገድ
  • አስተዳደራዊ ጥፋቶችና በደል አስመልክቶ የሚቀርቡ ቅሬታዎች / አቤቱታዎች በመቀበልና  በመመርመር ውሣኔ መስጠት
  • የተሰጡ ውሳኔዎች ተፈጻሚነታቸውን መከታተል
  • በማህበራዊ ተጠያቂነት ተግባር በህዝብ ተሳትፎ አስተዳደራዊ ችግሮች እንዲፈቱ ማስቻል፤
  • ክፍተቶችን የለየ ስልጠና በተዋረድ ለሚገኙ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ አካላት ስልጠና ስጠት፤
  • የህዝብ ቅሬታ ማስተናገጃ ስርአቱን ማስተዋወቅ፤ግንዛቤ መፍጠር
  • የሚነሱ ቅሬታዎች በተነሱበት አካባቢ እንዲፈቱ መደገፍና መከታተል 
  • በመንግስት መስሪያ ቤቶች ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻልና የተጠያቂነት ስርአትን ለመዘርጋት ህዝቡን ያሳተፈ የቁጥጥር አገልግሎት መስጠት 
  • በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ያለውን የቅሬታ አዝማሚያ በመመለከት  የተደራጁ መረጃዎችን መስጠት
Scroll to Top