Plan & Dev’t Team

የልማት ዕቅድ  ክትትልና ግምግማ ቡድን ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴቶች

ዞናዊ የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት ያለው ውስን የማስፈጸሚያ ሀብት ውጤታማ በሆኑ የልማት ሥራዎች ላይ ተመድቦ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የዞኑንን ህዝብ በልማት እኩል ተሳታፊና ፍትሃዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፈጣን መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት፣ ዘላቂ ልማት ማረጋገጥና ድህነትን ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ፡፡

ራዕይ

በ2025 ኢኮኖሚውን በረጅም ጊዜ ዕይታ በመምራት፣ ዜጎችን እኩል የልማት ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ በማድረግ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥና ድህነትን ለማጥፋት የልህቀት ማዕከል መሆን፡፡

እሴቶች

የስራ ቡድኑ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የእለት ከእለት ተግባሩን ለማከናወን በሚከተሉት  እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

  • ቅንነት
  • የሙያ ታማኝነት፣
  • የሕዝብ አገልጋይነት፣
  • ብቃትና የቡድን ሥራ፣
  • ለውጤትና ስኬት አልሞ መስራት፣
  • ለጋራ ዕድገትና መዋቅራዊ ለውጥ መትጋት፣
  • ለደንበኞች ዕርካታና ለሀገር ገጽታ ግንባታ መቆርቆር፣

      የልማት ዕቅድ  ክትትልና ግምግማ ቡድን አላማን ለማሳካት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • የክልሉን ማክሮ ኢኮኖሚ መእቀፍ መሰረት በማድረግ የዞኑን መሪ/ማክሮ እቅድ ማዘጋጀት፤ የእቅድ ዝግጅትና ቅንብርን በማስተባበር የአቅም ግንባታ ስልጠና ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፣ የዞኑንን የዕቅድ አፈፃፀምና ፍትሃዊ የሀብት አጠቃቀም  እንዲኖር አሥተዋፅኦ ማድረግ፡፡
  • ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን መሰብሰብና መተንተን፣ ጥናቶችን በማካሄድ የዞኑን አመታዊ ስታትስቲካል አብስትራክት እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮፋይል በማዘጋጀት  ለተጠቃሚዎች ማድረስ፡፡
  • ለልማት እቅድ ዝግጅት፣ ለስነ-ህዝብና ልማት ምርምር አጀንዳ፣ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ ጥናቶች፣ ለተለያዩ የስነህዝብና ልማት ሰነዶች ዝግጅት ወቅታዊና ደረጃቸውን የጠበቁ የስነ-ህዝብና ልማት መረጃዎች እንዲቀርቡ ዕገዛ ማድረግ፡፡
  • የፖሊሲ ረቂቆች ደረጃቸዉን የጠበቁ መሆነቸዉን ማረጋገጥ፣ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ በመገምገም ግብረ መልስ መስጠት፣ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የየሩብ ዓመቱ ሪፖርት መገምገም፣ የሱፐርቪዥን ስራ በማከናወንና የሚቀርቡ ጥቆማና ቅሬታዎች በማጣረት አስፈጻሚ አካላት በፖሊሲዎችና በስትራቴጂዎች መሰረት ተልዕኳቸውን እየተወጡ ስለመሆናቸው መከታተል፣ ውቅቱን የጠበቀ መረጃና የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ የዘርፉን ሥራ ውጤታማ ማድረግ፡፡
  • የስታትስቲካል  መረጃ ፍላጎት በመለየት ጥናት ማድረግ፣  የመረጃ ጥራት እንዲጠበቅ በማድረግ  መመሪያዎችና ተያያዥ ሰነዶችን ማዘጋጀት፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ወቅታዊ ጥራቱን የጠበቀና ተአማኒነት ያለው ስታትስቲካዊ መረጃ ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡

የሥራ ዘርፍ/ የሥራ ሂደት  የልማት ዕቅድ  ክትትልና ግምግማ ቡድን

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡-  የልማት ዕቅድ ክትትልና ግምግማ ቡድን መሪ

የሥራ መደቡ ዓላማ፡- የቡድኑን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበርና በመምራት;አጠቃላይ የክልሉን ማክሮ ኢኮኖሚ መእቀፍ መሰረት በማድረግ የዞኑን እቅድ በማዘጋጀት፤ የእቅድ ዝግጅትና ቅንብርን በማስተባበር ፤የአቅም ግንባታ ስልጠና ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት የዞኑንን የዕቅድ አፈፃፀምና ፍትሃዊ የሀብት አጠቃቀም  እንዲኖር አሥተዋፅኦ ማድረግ ነው፡፡

ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት 1፡ የቡድኑን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበርና መምራት፤

  • የቡድኑን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበር፤ መምራት፤ መቋጣጠርና ለአስቸኳይ ጉዳይ ውሳኔ ይሰጣል ፣
  • የቡድኑን ሥራ እቅድ ያዘጋጀል፤ ለቡድኑ ባለሙያዎች ሥራ ያከፋፍላል፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
  • የቡድኑን የሚከናወኑ ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወጪና ጥራት መሰረት መከናወናቸውን ይገመግማል፣ ያረጋግጣል፣
  • በቡድኑ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችና ችግሮችን በመገምገም ያሻሽላል፤
  • የባለሙያዎችን የውጤት ተኮር ዕቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን በየወቅቱ ይመዝናል፣ ይገመግማል፣
  • የቡድኑ ባለሙያዎች የተሟላ ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸውን ሃላፊነነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ዘላቂ የሰው ሃይል ልማት እንዲኖር ያደርጋል፤

ውጤት  2:  የልማታዊ እቅድ ዝግጅትና ቅንብር ማስተባበር

  • አጠቃላይ የዞኑን ማክሮ ኢኮኖሚ ማእቀፍ እቅድ በመምራት ያስተባብራል፤
  • የዞኑን የአጭር፤የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የልማት እቅድ ለመዘጋጀት የሚያስችል የእቅድ ዝግጅት መመሪያና ፎርማቶች እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
  • የዞኑን የብዙ አመት ማክሮ ኢኮኖሚ መእቀፍ እቅድ ቅንብር ያስተባብራል፤
  • የዞኑን ሴክተር መስሪያ በቶች የረጅም ጊዜ የልማት እቅድ ሲያዘጋጁ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
  •  የዞኑን የወረደና የከተማ አስተዳድር የረጅም ጊዜ የልማት እቅድ ሲያዘጋጁ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
  • የዞኑን አምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርማሽን እቅድ በማቀናባበር ለቅርብ ሃላፊ ያቀርባል፤
  • የዞኑን ሴክተር መ/ቤቶች የአመቱን እቅድ ሂደት ይከታተላል፤
  • የዞኑን ሴክተር መ/ቤቶች የሚያቀርቡት የትላልቅ ካፒታል ፕሮጀክት ፕሮፓዛል በመንግሥት ልማታዊ አቅጣጫ መሆኑን በመከታተል ያረጋግጣል፤
  • የዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች የአመት እቅድ እንዲቀናበር በማድረግ ለቅርብ ሃላፊ ያቀርባል፤
  •  የዞኑን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድር የአመት እቅድ እንዲቀናበር በማድረግ ለቅርብ ሃላፊ ያቀርባል፤

 ውጤት 3:- የአቅም ግንባታ ስልጠና ሙያዊ ድጋፍ መስጠት:

  • የዞኑን የአጭር፤ የመከካለኛና የረጅም እቅዶች  ከልማታዊ ፓሊሲ አቅጣጫ መመሪያዎችና ማኑዋሎችን ከክልል፤ ከፌደራል ልማታዊ ማክሮ ኢኮኖሚና ከአለም አቀፍ ልማት አጀንዳ ጋር በማጣጣም የተዘጋጀ መሆኑን ያረጋግጣል፤
  • በስትሬታጂካዊ ልማት እቅድ ላይ የስልጠና ማኑዋል እንዲዘጋጅ ያመቻቻል፤
  • በልማት ፓሊሲና በእቅድ ዝግጅት ቴክኒክ ላይ ሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤

የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት የልማት ዕቅድ ክትትልና ግምግማ ቡድን

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡-ሶሽዮ ኢኮኖሚስት

የሥራ መደቡ ዓላማ፡- ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን መሰብሰብና በመተንተን፣ ጥናቶችን በማካሄድ የዞኑን አመታዊ ስታትስቲካል አብስትራክት እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮፋይል በማዘጋጀት  ለተጠቃሚዎች ለማድረስ  ነው፡፡

  • ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት- 1.  ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች መሰብሰብ እና መተንተን፣ ጥናቶችን ማካሄድ፣

  • በፕሮግራሙ ወይም በፕሮጀክቱ ያልተዳሰሱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶችን ይለያል፣ በጋራ በማዘጋጀት ያጠናል፣
  • የፕሮግራሞችንና የፕሮጀክቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ ሃሳቦችን ያመነጫል፤
  • የማህበራዊ ኢኮኖሚ የልማት አመላካቾችን ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በማጣጣም  ጥናትና ትንተና ያደርጋል፤
  • ዞናዊ ጥቅምን ማስከበር የሚችሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች፤
  • በተቋሙ ውስጥ በተለያየ ዘርፍ በሚካሄዱና አስፈላጊ በሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናቶችን  ያካሄዳል፣
  • ከተቋሙ ጋር አግባብነት ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ይሰበስባል፤
  • ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ የዞኑን የምግብ ዋስትናና የደህንነት ሁኔታ ጥናቶች ያካሂዳል፤ የጥናት ውጤቶችንም ለባለ ድርሻ አካላት ያደርሳል፣

ውጤት- 2.  አመታዊ  ስታትስቲካል አብስትራክት እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮፋይል  ማዘጋጀትና ለተጠቃሚዎች ማድረስ፣

  • የሚሰበሰቡ የመረጃ ዓይነቶችን በመለየት የተለያዩ ፎርማቶችን በማዘጋጀት በየደረጃው በማውረድ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ያደርጋል፣
  • የአመታዊ ስታትስቲካል አብስትራክት በማዘጋጀት ለተጠቃሚው ያደርሳል፣
  • የልማት አመልካች መጽሔት በማዘጋጀት ለተጠቃሚው ያደርሳል፣
  • የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮፋይል በማዘጋጀት ለተጠቃሚው ያደርሳል፣
  • የዞኑን መረጃ በዌብ ሳይት በመልቀቅ ለተጠቃሚው ያደርሳል፣
  • የተለያዩ ዳታ ቤዞችን በመጠቀም መረጃዎችን አደራጅቶ ለተጠቃሚው ያደርሳል፣
  • Amhara infoን ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለው መረጃ ተሰብስቦ ለተጠቃሚ እንዲደርስ ያደርጋል፣
  • Amhara infoን በየጊዜው ወቅታዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • ለተጠቃሚዎች ቀላል የAmhara infoን ዌብ ሳይትና Application ፕሮግራም በማዘጋጀት ዳታ ቤዙን እንዲጠቀሙ ያደርጋል፣

የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት የልማት ዕቅድ  ክትትልና ግምግማ ቡድን

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡-የሥነ-ሕዝብ ጥናትና መረጃ ባለሙያ

የሥራ መደቡ ዓላማ፡- ለልማት እቅድ ዝግጅት፣ ለስነ-ህዝብና ልማት ምርምር አጀንዳ፣ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ ጥናቶች፣ ለተለያዩ የስነህዝብና ልማት ሰነዶች ዝግጅት ወቅታዊና ደረጃቸውን የጠበቁ የስነ-ህዝብና ልማት መረጃዎች እንዲቀርቡ ዕገዛ ማድረግ ነው፡፡

ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት-1፡– ለዞኑ በሎም ለክልሉና ለሃገሪቱ የረጅም፣ መካከለኛና አጭር ዘመን እቅድ ዝግጅት እና ለሥነ- ሕዝብና ልማት ጥናትና ሰነዶች ዝግጅት የሚውሉ መረጃዎች መለየት፣ በማጠናቀርና በማመሳከር ድጋፍ ማድረግ፡፡

  • የዞኑን በሎም የክልሉና የአገሪቱን ዲሞግራፊ ባህሪያት አዝማሚያ የሚያሳዩ መረጃዎችና ጥናቶች ያጠናቅራል፣ መረጃዎችን በማጣራት ትክክኛነት ያረጋግጣል፡፡
  • ለረጅም፣ ለመካከለኛ እና ለአጭር ዘመን ፕላን ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ ለሥነ-ሕዝብ ትንበያዎች የሚረዱ ሥነ-ሕዝብ ነክ መረጃዎችን ያጠናቅራል፣ የመረጃውን ትክክልኛነት ያመሳክራል፣ያረጋግጣል፡፡
  • ከሥነ-ሕዝብና ልማት ጋር የተገናኙ ጥናቶች እንዲካሄዱ መረጃዎችን ያጠናቅራል፣ በምርምር አጀንዳ ዝግጅት ላይ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፡
  • የልደት የጋብቻ የሞትና የአድራሻ ለውጥ ወዘተ…. የመሳሰሉት ዋና ዋና ክስተቶች የሚመዘገቡበት ሀገር አቀፍ ሥርዓት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ የተሰበሰበውን መረጃ ያጠናቅራል፡፡
  • ኅብረተሰቡ የሥነ-ሕዝብና ልማት መረጃዎችን የማግኘትና የመጠቀም ዕድሉ ከፍ እንዲል ለማድረግ የኢንፎርሜሽን፣ ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ዝግጅት የተሰበሰቡ መረጃዎችን ያጠናቅራል፣ የመረጃዎችን ትክክልኝነት ያረጋግጣል፡፡
  • ለሥነ-ህዝብና ልማት መጽሄት ዝግጅት ጽሁፍ የሚዘጋጅባቸውን የተመረጡ ርእሶችን በተለያዩ የማስታወቂያ ቦታዎችና ተቋሞች ውስጥ ይለጥፋል ወይም እንዲለጠፍ ያደርጋል፣ በተለያዩ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና አካላት ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ጽሁፎችን ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ይለያል ፡፡
  • ለስነ-ህዝብና ልማት አመልካች፣ የኢትዮጵያ ዲሞግረፊና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮፋይል(Demographic and Socio Economic Profile of Ethiopia)፣ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ ትንተና ሁኔታ (Population Situation Analysis of Ethiopia) እና ሌሎችንም ዝግጅት መረጃችን ያደራጃል፡፡
  • በተለያዩ የሥነ-ሕዝብና ልማት ዘርፎች ትግበራ ላይ የተሰማሩትን ድርጅቶች (መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ) ይለያል፣ መረጃ ያደራጃል፡፡
  • የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ መረጃዎችን ያጠናቅራል የመረጃዎችን ትክክልኝነት ያረጋግጣል፡፡
  • አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሥነ-ሕዝብና ልማት ጉዳዮችንና እንድምታውን ለመከታተል መረጃዎችን ይለያል፣ ያጠንቅራል፡፡
  • የሥነ-ሕዝብ ባለሙያዎች ስልጠና ከከፍተኛ ትምህርትና ከሥራ ሥምሪት አንጻር መሆኑን መረጃ ያጠናቅራል፣ የመረጃዎችን ትክክልኝነት ያረጋግጣል፡፡
  • የራሱን እቅድ ያዘጋጃል፣ በቡድን እቅድ ዝግጅት ወቅት ይሳተፋል፣ ዕቅዱን ይፈጽማል፣ ሪፖርት በማዘጋጀት ለኃላፊው ያቀርባል፡፡

ውጤት-2 የተዘጋጁ የሥነ-ህዝብና ልማት መረጃዎች ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረግ የህብረተሱቡ ግንዛቤ ክፍ እንዲል አስተዋጽ ማድረግ፡፡

  • ኅብረተሰቡ የሥነ-ሕዝብና ልማት መረጃዎችን የማግኘትና የመጠቀም ዕድሉ ከፍ እንዲል ለማድረግ የተዘጋጀውን የኢንፎርሜሽን፣ ትምሕርትና ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
  • በስነ-ህዝብና ልማት ዙሪያ በሚመጡ የግንዛቤ ለዉጦች ለመገምገም በሚደረገው ሂደት ላይ በመሳተፍ ግብአት ይሰጣል፡፡
  • የተዘጋጁ የሥነ-ህዝብና ልማት መረጃና ጥናቶች ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፡፡
  • የሥነ-ሕዝብ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ሲምፖዚየም ስብሰባዎች ዓውደ ጥናቶች እና ሥልጠናዎች በዞንና በወረዳዎች እንደዚሁም በከተማ አስተዳደሮች  ውስጥ እንዲዘጋጁ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ እገዛያ ደርጋል፡፡

 የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት የልማት ዕቅድ ክትትልና ግምግማ ቡድን

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡-የፖሊሲና ዕቅድ አፈፃፀም ክትትል ባለሙያ

የሥራ መደቡ ዓላማ፡-የፖሊሲ ረቂቆች ደረጃቸዉን የጠበቁ መሆነቸዉን በማረጋገጥ፣ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ በመገምገም ግብረ መልስ መስጠት፣ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የየሩብ ዓመቱ ሪፖርት በመገምገም፣ የሱፐርቪዥን ስራ በማከናወንና የሚቀርቡ ጥቆማና ቅሬታዎች በማጣረት አስፈጻሚ አካላት በፖሊሲዎችና በስትራቴጂዎች መሰረት ተልዕኳቸውን እየተወጡ ስለመሆናቸው መከታተል፣ ውቅቱን የጠበቀ መረጃና የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ የዘርፉን ሥራ ውጤታማ ማድረግ፡፡

ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት-1፡ የፖሊሲ ረቂቆች ደረጃቸዉን የጠበቁ መሆነቸዉን ማረጋገጥ

  • ለዞን አመራሩ የሚቀርቡ የአፈጻጸም ሪፖርቶች ደረጃቸዉን የጠበቁ መሆናቸዉን ያረጋግጣል:-
  • የሚቀርቡ ሪፖርቶች ከመ/ቤቶች ሥልጣንና ተግባር ጋር የተቆራኘ መሆኑን ያረጋገጣል፤
  • ከአገራዊና ክልላዊ  ህገ መንግስትና ከፖሊሲና ስትራቴጂዎች ጋር በማነጻፀር ክፍተቶችን ይለያል፤

ውጤት- 2፡ የአስፈጻሚ መስሪያቤቶችን ዕቅድ በመገምገም ግብረ መልስ መስጠት፤

  • የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ በመገምገም ግብረ- መልስ ይሰጣል፤
  • የዕቅዱን ክፍተቶች በመገምገም ግብረመልስ በመስጠት ማግባባት ይፈጥራል፤
  • የተሰጠዉን ግብዓት መሰረት ማስተካከያዎቹ በዕቅዱ ውስጥ መካተቱን ያረጋግጣል፤

ውጤት -3፡የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የየሩብ ዓመቱ ሪፖርት መገምገም፤

  • የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የየሩብ ዓመቱ ሪፖርት ይገመግማል
    • ከአገራዊ የልማት ዕቅድ ስትራቴጂዎችና ከበጀት ዓመቱ ዕቅድ ጋር በማነፃፀር ክፍተቶችን ይለያል
    •  በተለዩት ክፍተቶች ላይ ግብረ-መልስ በማሰጠት ማግባባት ይፈጥራል

ውጤት- 4፡ የሱፐርቪዥን ስራ ማከናወን፤

  • ቼክሊስት ለማዘጋጀት መረጃ ይሰበስባል፤
    • የመስክ ስራ ዕቅድና ቼክሊስት ያዘጋጃል፤
    • ከሚመለከታቸዉ ባለድረሻ አካላት ጋር ዉይይት በማድረግ መግባባት ለመፍጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
    • የሱፐርቪዥን ስራ ያከናውናል፤
    • ሥራዎች በቼክሊስቱ መሰረት መከናወኑን ያረጋግጣል፤
    • ባለድርሻ አከላት(አስፈጻሚና ተጠቀሚ ህብረተሰብ) ያወያያል፤
    • በየደረጃ ላለዉ አስፈጻሚና ለሚመለከተዉ አከላት ግብረ መልስ ይሰጣል፤
    • የሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት በማዘጋጀት ለበላይ አመራር ያቀርባል፤
    • የዞን አስተደዳር ዕቅድ ዝግጅትና የዕቅድ አፈፀፃም የጋራ ግምገማ መድረክ ላይ ይሳተፋል፣ አስፈለጊዉን ግብዓት ይሰጣል፤
    • በዉይይት ላይ የተነሱ ጠንከራና ደካማ ጐን ይለያል፤
    • የዉይይቱን ማጠቃለያ ሪፖርት በማዘጋጀት ያቀርባል፤
  • ለተገልጋዮችና ለባለድርሻ አካላት ግብረ-መልስ ይሠጣል፤

ውጤት -5፡-ለዞን አስተዳዳሪውና ለየዘርፉ የሚቀርቡ ጥቆማና ቅሬታዎችን ማጣራት

  • ከሚመለከተዉ  አካል ጋር ዉይይት በማድረግ ቅሬተዉን ይመረምራል፤
  • አጠቃላይ ጥቆማና ቅሬታዎችን በማጣራት የመፍተሄ ሃሳብ በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
  • ለቅሬታዉ ወይም ጥቆማ አቅራቢ አካል ግብረመልስ ይሰጣል፤
  • በዘርፉና ዘርፉ ድጋፍ በሚያደርግባቸዉ አስፈጻሚ መ/ቤቶች የሚያጋጥሙ ችግሮች የሚፈቱበት ጥናት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ያካሄዳል፡፡
  • በጥናቱ የተመለከቱ መፍትሔዎች በአግባቡ ተግባራዊ መደረጋቸዉና ችግሮቹ መቀረፋቸዉን ይከታተላል፡፡

የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት የልማት ዕቅድ ክትትልና ግምግማ ቡድን

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡-የስታቲስቲካል ዳታ ስርዓት አስተዳደርና ትንተና ባለሙያ

የሥራ መደቡ ዓላማ፡- የስታትስቲካል  መረጃ ፍላጎት በመለየት ጥናት በማድረግ፣  የመረጃ ጥራት እንዲጠበቅ በማድረግ እና መመሪያዎችና ተያያዥ ሰነዶችን በማዘጋጀት ፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ወቅታዊ፣ ጥራቱን የጠበቀና ተአማኒነት ያለው ስታትስቲካዊ መረጃ ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡

ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ዉጤት- 1.የስታትስቲካል መረጃ ፍላጎት መለየትና ጥናት ማድረግ

  • ለስታትስቲካል ዳታ ፍላጎት ማሰባሰቢያ የተዘጋጁ መጠይቆች የተሟሉና ስታንደርዳቸዉን የጠበቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
  • የመረጃ ማሰባሰቢያ መጠይቆች/ቅጾች/ ስታንዳርድና ስፕስፊክሽን ዝግጅት ሥራ ያከናዉናል፣
  • የመረጃ ማሰባሰቢያ መጠይቆች/ቅጾች/ በተዘጋጀላቸዉ ስታንዳርድና ስፔስፊኬሽን መሰረት ለህትመት እንዲዘጋጁ ድጋፍ ያደርጋል
  • የተዘጋጁ የመረጃ ማሰባሰቢያ መጠይቆችን እንደ የመረጃ ባህሪዉ ተለይቶ እንዲደራጅ ግብአት ይሰጣል፣ተጣርተዉ በተዘጋጁ የፍላጎት ማሰባሰቢያ መጠይቆች  ላይ ትንተና ያዘጋጃል፣
  • የስታቲሰቲካል ዳታ ክፍተት ያለበትን አካባቢ ይለያል፣ በተገኙ ክፍተቶች ላይ ጥናት የሚከናንበትን ዘዴ በማቀነባበር ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተዉ አካል በማቅረብ ስለ አተገባበሩ ዉሳኔ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ለስታቲሰቲካል ዳታ ጥናት ተግባር አስፈላጊዉ የአቅም ግንባታ ስራ፤ የሰዉ ሀይል፤ የስራ ቁሳቁስ ሎጂስቲክና በጀት  የሚሟላበትን ስልት በመቀየስ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣
  • ፖሊሲ ለመንደፍና ለዉሳኔ አስፈላጊ የሆኑ የስታትስቲካዊ መረጃ ጋር ቁርኝት ያላቸዉን  የከተሞች ሥራ ስምሪት ምጣኔ፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስርጭት የክልሉን ልማት የእድገት  ክፍተት የሚያሳዩ ጥናቶችን ያከናዉናል፣
  • በመረጃ አሰባሰብ፣አስተዳደርና አጠቃቀም ምርጥ ተሞክሮችን ይቀምራል፣
  • ለተለያየ ዶክመንት ዝግጅት በሚያመች መንገድ ተለይተዉ ከተደራጁት የሰታቲስቲካል መረጃዎች ዉስጥ የዓመታዊ  የስታቲስቲካል አብስትራክ ዶክመንት፤ የዞናዊ የተከታታይ ዓመታት መረጃ ዶክመንት  የሀብት ክፍፍል /ቀመር/ መረጃ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ግምገም መረጃ ዶክመንት ያዘጋጃል፣
  • ተተንትነዉ የተዘጋጁ ዶክመንቶችን ለህትመት ዝግጁ የማድረግ፤ የካሜራ ሬዲ ሥራዎች፤ የህትመት ስፔሲፊኬሽን ዝግጅትና የዶክመንት ህትመት ተግባራትን ይደግፋ ፣ ተደራሽነቱንም ይከታተላል

ዉጤት- 2. መረጃዎችን ማደራጀትና  መተንተን

  • ከየአስተዳደር እርከኑ የተሰበሰቡ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ  መረጃዎች ከየዘርፉ መሰባሰቡን ያረጋግጣል፣ በስታንዳርዱ መሰረት ያደራጃል ፣
  • በየደረጃዉ የተሰባሰቡ መረጃዎች ጥራታቸዉን በጠበቀ መልኩ ይለያል፣ ያደራጃል፣ በዳታ ቤዝ ገብተዉ በየደረጃዉ እንዲደራጁ ያደርጋል፣
  • በመረጃ ቋት/ዳታቤዝ/ ገብተዉ የተደራጁ መረጃዎች ለተለያየ ተግባር ሊዉል በሚችል መንገድና ስልት ይቀይሳል፣ ለተለያዩ ዶክመንት ዝግጅት በሚያመች መንገድ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣
  • የስታቲስቲካል ዳታ አሰባሰብ፤ አደረጃጀት፤ ትንተና፣ ስርጭት  ዜዴዎች እና  የዳታቤዝ አስተዳደርና አጠቃቀም ደንብ፣ መመሪያና ማኑዋሎችን  ዝግጅት ላይ  ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣

ዉጤት-3. ክትትልና  ድጋፍ ማድረግ

  • በየደረጃው በሚገኙ አስተዳደራዊ መዋቅር ባሉ መሥሪያ ቤቶች የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች በመረጃ አሰባሰብ፤ አደረጃጀት፤ አጠቃቀምና ትንተና ዘዴዎች ላይ የሚታዩትን የአቅም ክፍተቶች ይለያል፣ አቅማቸውን ለመገንባትና ለመደገፍ ሀሳብ ያቀርባል፣
  • ባለሙያዎች በመረጃ አሰባሰብ፤ አደረጃጀት፤ አጠቃቀምና ትንተና ዜዴዎች ላይ በተለዩ ክፍተቶች  ስልጠና ለመስጠት የሥልጠና ማኑዋል ያዘጋጃል፣ ስልጠና ይሰጣል፣ የስልጠና ሂደትንም ያስተባብራል፣

Scroll to Top